Duck hunt
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

PicsArt 1440869880774

App full proxy-5 10

ጥያቄና መልስ
ደረጃ አንድ

የሚከተለውን ኢስላማዊ ጥያቄና መልስ ታናናሽ ወንድሞቻችነን እና እህቶቻችነን ወይም የጐረቤታችንን ልጆች በመጠየቅ ስለ ኢስላም ያላቸውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ እንሞክር!!!
ይህን አስባችሁ ከታናሻችሁ ጋር ሼር የምታረጉ ሁሉ አሏህ በመልካም ነገር ይመንዳችሁ። ይህ ጥያቄ የተዘጋጀው ታናናሽ ወንድሞቼን እና እህቶቼን ታሳቢ በማድረግ ነው።


App full proxy-5 11
QandA 1

1 እምንሰራውን ስራ የሚመዘግቡ መላአክቶችን ምን ብለንነው የምንጠራቸው?

ሀ) ኢስራፊል

ለ) ኪራመን ካቲቢን

ሐ) መላኢካ

መ) ኢዝራኢል

2 የኢስላም ምሶሶዎች ምን በመባል ይጠራሉ?

ሀ) ቀድሩል ኢስላም

ለ) አርካነል ኢስላም

ሐ) ዩሱፍ ኢስላም

መ) ፊአማኒላህ

3 ነብይ በአረብኛ___________በመባል ይጠራል?

ሀ) ረሱል

ለ) ወህይ

ሐ) አውሊያ አሏህ

መ) መልሱ የለም

4 ኢስላም ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ) አሏህን ማክበርና ለትእዛዙ ተገዥ መሆን

ለ) ቤተሰብን ማክበር

ሐ) አስተማሪዎቻችነን እና ታላላቆቻችነን ማክበር

መ) መልሱ የለም

5 አሏህ__________

ሀ) ወንድ ልጅ አለው

ለ) ቤተሰብ አለው

ሐ) አጋር የለውም

መ) ሴት ልጅ አለው

6 ስንት አሏህ አለ?
ሀ) 3

ለ) 2

ሐ) 1

መ) 0

7 መሬትን፣ሰማይን፣ፀሀይን፣ጨረቃንና ከዋክብቶችን፣ኮረብታዎችን፣ወንዞችን፣አበባዎችን ወ.ዘ.ተ የፈጠረ ማንነው?

ሀ) ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)

ለ) አደም(ዐ.ሰ)

ሐ) አሏህ

መ) ሁሉም መልስ ናቸው።

8 ስታነጥስ ምንድ ነው የምትለው?

ሀ) የርሀሙከሏህ

ለ) ያ አሏህ

ሐ) አልሐምዱ ሊላህ

መ) ላ ኢላሀ ኢለሏህ

9 በኢስላም ካላንደር የመጀመሪያው ወር ማን ነው?

ሀ) ሙሐረም

ለ) ረመዷን

ሐ) ሸዋል

መ) ረቢኡል አወል

10 ሶላት ምንድ ነው?

ሀ) መፆም

ለ) ድሆችን መርዳት

ሐ) ስግደት

መ) ሀጅ

11 የቁርአን ቇንቇ___________ነው?

ሀ) እንግሊዘኛ

ለ) አረብኛ

ሐ) ህንደኛ

መ) ይብራይስጥኛ

12 አረህማን ማለት__________ማለት ነው?

ሀ) ሁሉን አዋቂ

ሀ) ሀያሉ

ሐ) በጣም ርህሩህ

መ) ሁሉም መልስ ናቸው

13 የመጀመሪያው የአሏህ(ሱ.ወ.ተ) መልእክተኛ___________ ነበር?

ሀ) ኑህ (ዐ.ሰ)

ለ) ሁድ (ዐ.ሰ)

ሐ) አደም (ዐ.ሰ)

መ) ሙሳ (ዐ.ሰ)

14 ለነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የተላከው መጽሐፍ ስም___________ነው?

ሀ) ኢንጂል

ለ) አል-ቁርአን

ሐ) ተውራት

መ) ዘቡር

15 ሱራ አል-አስር በተመለከተ «በእውነቱ የሰው ልጆች በእጦት(በውድቀት) ላይ ናቸው፤እነዚያ_________ሲቀሩ።»

ሀ) ኢማን ያላቸው

ለ) መልካም ሰሪዎች

ሐ) እውነቱን ለመከተል እርሰ በርስ የሚደጋገፉና በመልካም ስራዎች ላይ ተሽቀዳዳሚ የሆኑ

መ) ሁሉም መልስ ናቸው

16 «አንተን ብቻ ነው የምንገዛ ፤አንተንም ብቻ ነው እርዳታ የምንጠይቀው።»
ይህ የቁርአን አንቀጽ ከየትኛው ሱራ ነው?

ሀ) አል-ኢህላስ

ለ) አል-ፋቲሐ

ሐ) አል-ከውሰር

መ) አል-አስር

17 አናስ ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ) ንጋት

ለ) መክፈቻ

ሐ) ሰዎች

መ) ምሽት

18 የአል-ፈለቅ ትርጉም ምንድ ነው?

ሀ) ንጋት

ለ) ሰዎች

ሐ) መክፈቻ

መ) ድል

19 አል-ፊል ምን ማለት ነው?

ሀ) ዝሆን

ለ) ሸረሪት

ሐ) አንበሳ

መ) ዘንዶ

20 የቁርአን መክፈቻ ሱራ የትኛው ነው?

ሀ) አል-ከውሰር

ለ) አል-ፋቲሐ

ሐ) አል-አስር

መ) ሁሉም መልስ ናቸው

21 የአስተግፊሩሏህ ትርጉም ምንድነው?

ሀ) የአሏህን ምህረት እጠይቃለሁ

ለ) ወደ አሏህ ተመላሾች ነን

ሐ) ዱአችነን ተቀበለን

መ) መልሱ የለም

22 የአንድ ሙስሊም ሰው የመጀመሪያ ግዴታው ምንድነው?

ሀ) ሶላት

ለ) ፆም

ሐ) ሀጅ

መ) ሸሐዳ

23 የሶላት አንዷ ክፍል ምን ተብላ ትጠራለች?

ሀ) ፈርድ

ለ) ረከአ

ሐ) ጁዝእ

መ) ሱና

24 ዘካን መክፍል ያለብን በምንድን ላይ ነው?

ሀ) በገንዝብ

ለ) በጌጣጌጥ

ሐ) በቀንድ ከብቶች

መ) ሁሉም መልስ ናቸው

25 «በል እርሱ አሏህ አንድ ነው።አሏህ ዘላለማዊ ነው።አልወለደም፣አልተወለደም፣አምሳያም የለውም።»
የሚለው የቁርአን ሱራ___________ ነው?

ሀ) አል-ኢህላስ

ለ) አል-ፋቲሐ

ሐ) አል-ከውስር

መ) አል-ናስ

26 ኢማን ማለት____________

ሀ) በአሏህ ማመን

ለ) በመጽሐፎቹ ማመን

ሐ) በመልእክተኞቹ ማመን

መ) ሁሉም መልስ ናቸው

27 የፈጅር፣የዙሁር፣የአስር፣የመግሪብ እና የኢሻ ሶላቶች___________ናቸው?

ሀ) ሱና

ለ) ነፍል

ሐ) ዋጅብ

መ) መልሱ የለም

28 የሶላት አላማ ምንድ ነው?

ሀ) አሏህን ለማስታወስ እና ከአሏህ ጋር ያለንን ትስስር ለማጠንከር

ለ) ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወን ለማስታወስ

ሐ) መልሱ የለም

29 መቼ ነው የዊትር ሶላት የሚሰገደው?

ሀ) ከፈጅር ሶላት ብኋላ

ለ) ከኢሻ ብኋላ

ሐ) ከመግሪብ ብኋላ

መ) ከዝሁር ብኋላ

30 በመካ የሚገኘው የአሏህ ቤት____________በመባል ይጠራል?

ሀ) ቤተ-ክርስቲያን

ለ) መስጅደል አቅሷ

ሐ) ካእባ

መ) መስጅደ ነበውይ

31 ለምን ያህል ጊዜ ነው ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የሰበኩት?

ሀ) ለ 23 ዓመታት

ለ) ለ 32 ዓመታት

ሐ) ለ 40 ዓመታት

መ) ለ 14 ዓመታት

32 አሏህን የካዱ ሰዎች ወደ___________በመላክ በአሰቃቂ ሁኔታ ይቀጣሉ?

ሀ) እስር ቤት

ለ) ጀሐነም

ሐ) ፍርድ ቤት

መ) ጀነት

33 የሸሐዳ ትርጉም ምንድነው?

ሀ) ከአሏህ በቀር ሊያመልኩት የሚገባ አምላክ አለመኖሩንና ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር

ለ) አሏህ አንድ ነው መልእክተኛው ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ልጁ ነው ብሎ መመስከር

ሐ) ሙሐመድ አምላክ ነው ብ ሎ መመስከር

መ) ሁሉም መልስ ናቸው

34 ጀነት የ__________ቦታ ነው?

ሀ) የንዴት

ለ) የርሀብና የጥማት

ሐ) የስቃይ

መ) የምቾትና የደስታ

35 በረመዷን ወር ከአንድሺ ወራቶች በላይ የሆነ ምሽት አለ።ይህም____________በመባል ይጠራል?

ሀ) ቂያመ ለይል

ለ) ለይለቱል ቀድር

ሐ) ኢዱል ፊጥር

መ) መልሱ የለም

36 የፈጅር ሶላት የሚሰገደው መቼ ነው?

ሀ) ፀሀይ ስትጠልቅ

ለ) ፀሀይ ከጠለቀች ብኋላ

ሐ) ከሰአት ብኋላ

መ) ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት

37 ቢስሚላሂ ረህማኒ አረሂም ምን ማለት ነው?

38 ካእባ_____________በመባል ይጠራል?

39 በረመዷን ወር ፀሀይ ከመውጣቷና የፈጅር ሶላትን ከመስገዳችን በፊት የምንወስደው ምግብ ምን በመባል ይጠራል?

ሀ) ኢፍጣር

ለ) ሱሁር

ሐ) ተራዊህ

መ) ሁሉም መልስ ናቸው

40 የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) አባት ማን ነበሩ?

ሀ) አብዱሏህ

ለ) አብዱል ሙጠሊብ

ሐ) አቡ ጧሊብ

መ) ሐምዛ

41 ሀጅን ተከትሎ የሚመጣ በአል___________ነው?

ሀ) ኢዱል አዱሐ

ለ) ኢዱል ፊጥር

ሐ) አቂቃ

መ) ወሊማ

42 አንዱ የኢስላም ምሰሶ ድሆችን በገንዘብ መርዳት ነው።ይህ ምሰሶ ምን በመባል ይጠራል?

ሀ) ፆም

ለ) ሀጅ

ሐ) ሶላት

መ) ዘካት

43 በአስር ሶላት ስንት ረከአ ነው የምንሰግደው?

ሀ) 2

ለ) 3

ሐ) 4

መ) 6

44 ቁርአን____________?

ሀ) የነብዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ ቃል ነው

ለ) የታሪክ መፅሐፍ ነው

ሐ) የአሏህ ቃል ነው

መ) መልሱ የለም

45 የሂራ ዋሻ በየትኛው ተራራ ነው የሚገኘው?

ሀ) በኤቨረስት ተራራ

ለ) በሲናይ ተራራ

ሐ) በኑር ተራራ

መ) መልሱ የለም

46 ለነብዩ ኢብራሂም የተላከው መጽሐፍ ስም______________ነው?

ሀ) ተውራት

ለ) ዘቡር

ሐ) ኢንጅል

መ) መልሱ የለም


ጥያቄና መልስ ደረጃ አንድ
ጥያቄና መልስ ደረጃ 2
Iqra
Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra
Iqra
8184

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ